እንኳን ወደ አጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመረጃ ፖርታል በደህና መጡ !!!
ይህ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ 7/24 አገልግሎት የሚሰጥ ወቅታዊ መረጃ ማስተዳደሪያ ፖርታል ሲሆን በመረጃ ማስተዳደሪያ ፖርታሉ በከተማ አስተዳደር የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፤ መምህራን፤ ተማሪዎች ፤ትምህርት ቤት አመራሮችን እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ለትምህርት ማህበረሰቡ እና ለሌሎች አገልግሎት ፈላጊዎች ወቅታዊ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡
በመረጃ ማስተዳደሪያ ፖርታሉ የሚገኙ መረጃዎች ከክፍለ ከተሞች፤ ከወረዳዎችና ከትምህርት ቤቶች ተሰብስበው ትክክለኛነታቸዉ በሚመለከታቸው አካላት ተረጋግጦ የተጫኑ ሲሆን በተመሳሳይ የትምህርት መረጃዎቹ በቢሮዉ በሚገኙና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ዳይሬክቶሬቶች መረጃዎቹን ተተንትነው ለአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተላኩ ናቸው፡፡
የተዘጋጀዉ የመረጃ ማስተዳደሪያ ሲስተም አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተሰራዉ በሲስተሙ ዉስጥ ያለዉን መረጃ ማየትና ለመጠቀም ለተፈቀደላቸዉና ለተመዘገቡ አካላት ብቻ ነዉ፡፡ ሲስተሙን ለመጠቀም እባክዎ የአጠቃላይ ትምህር መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥሮች /0991151571, 0946316965, 0911885812 / ወይም /tayewkidan@gmail.com / ኢሜል ይላኩ፡፡
በሲስተሙ የተመዘገቡ ከሆነ በሲስተሙ ዉስጥ ያሉትን መረጃዎች ለመጠቀም እባክዎ ከአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የተሰጠዎትን “Username” እና “Password” መግቢያው ላይ ባለው ቦታ በጥንቃቄ በማስገባት ከዛም በቀጣይ ሲስተሙ አስታዉሶ በቀጥታ ወደ መረጃዎቹ እንዲወስዶት “Keep me signed in“ ከሚለዉን ጎን ያለዉን አራት ማዕዘን ቦክስ በመንካት“Login” የሚለዉን በመጫን ይግቡ፡፡
መረጃ ሐይል ነዉ !!!
የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
Educational Management Information System Directorate/EMIS/